ዘፀአት 23:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 “ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ አደርገዋለሁ።+ ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ።+ ዘኁልቁ 34:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “ለእስራኤላውያን ይህን መመሪያ ስጣቸው፦ ‘ወደ ከነአን ምድር ስትገቡ+ ርስት አድርጋችሁ የምትወርሷት ምድር ይኸውም የከነአን ምድር ከነወሰኖቿ ይህች ናት።+ ዘኁልቁ 34:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 “‘ምዕራባዊ ወሰናችሁ ደግሞ ታላቁ ባሕርና* የባሕሩ ዳርቻ ይሆናል። ይህ ምዕራባዊ ወሰናችሁ ይሆናል።+ ዘዳግም 11:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 እግራችሁ የረገጠው ቦታ ሁሉ የእናንተ ይሆናል።+ ወሰናችሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ሊባኖስ እንዲሁም ከወንዙ ይኸውም ከኤፍራጥስ ወንዝ አንስቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር* ድረስ ይሆናል።+
31 “ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ አደርገዋለሁ።+ ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ።+
24 እግራችሁ የረገጠው ቦታ ሁሉ የእናንተ ይሆናል።+ ወሰናችሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ሊባኖስ እንዲሁም ከወንዙ ይኸውም ከኤፍራጥስ ወንዝ አንስቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር* ድረስ ይሆናል።+