-
1 ነገሥት 4:34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
34 ስለ እሱ ጥበብ ሲወራ የሰሙ በተለያየ የምድር ክፍል የሚገኙ ነገሥታትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ብሔራት፣ ሰዎች የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ይመጡ ነበር።+
-
-
1 ነገሥት 10:4-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 የሳባ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ+ ሁሉና የሠራውን ቤት ስትመለከት፣+ 5 በገበታው ላይ የሚቀርበውን ምግብ፣+ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ፣ አስተናጋጆቹ በማዕድ ላይ የሚያስተናግዱበትን መንገድና አለባበሳቸውን፣ መጠጥ አሳላፊዎቹን እንዲሁም በይሖዋ ቤት ዘወትር የሚያቀርባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ስታይ በመገረም ፈዛ ቀረች።* 6 በመሆኑም ንጉሡን እንዲህ አለችው፦ “ስላከናወንካቸው ነገሮችና* ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ነገር እውነት ነው። 7 ይሁንና እኔ ራሴ መጥቼ በገዛ ዓይኔ እስከማይ ድረስ የተነገረኝን ነገር አላመንኩም ነበር። እንደዚያም ሆኖ ግማሹ እንኳ አልተነገረኝም! በጥበብም ሆነ በብልጽግና ከሰማሁት ሁሉ እጅግ የላቅክ ነህ።
-