-
ዘዳግም 4:40አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
40 ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁና አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ለረጅም ዘመን እንድትኖር እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ሥርዓትና ትእዛዛት ጠብቅ።”+
-
-
ዘዳግም 12:28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
28 “እኔ የማዝህን እነዚህን ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንላችሁ ነው።
-
-
ሮም 10:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ሙሴ በሕጉ አማካኝነት ስለሚገኘው ጽድቅ ሲገልጽ “እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል” ሲል ጽፏል።+
-