-
ምሳሌ 3:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚወቅስ ሁሉ
ይሖዋም የሚወዳቸውን ይወቅሳልና።+
-
-
ዕብራውያን 12:5-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ደግሞም ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን የተሰጣችሁን የሚከተለውን ማሳሰቢያ ሙሉ በሙሉ ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ* የሚሰጥህን ተግሣጽ አቅልለህ አትመልከት፤ በሚያርምህም ጊዜ ተስፋ አትቁረጥ፤ 6 ይሖዋ* የሚወዳቸውን ይገሥጻልና፤ እንዲያውም እንደ ልጁ አድርጎ የሚቀበለውን ሁሉ ይቀጣል።”*+
7 ተግሣጽ የምትቀበሉበት* አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ መከራ ሲደርስባችሁ መጽናት ያስፈልጋችኋል። አምላክ የያዛችሁ እንደ ልጆቹ አድርጎ ነው።+ ለመሆኑ አባቱ የማይገሥጸው ልጅ ማን ነው?+
-