-
ኢያሱ 8:33, 34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
33 እስራኤላውያን በሙሉ፣ ሽማግሌዎቻቸው፣ አለቆቻቸውና ዳኞቻቸው የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት በሚሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ከታቦቱ ወዲህና ወዲያ ቆመው ነበር። የባዕድ አገር ሰዎችም ሆኑ የአገሬው ተወላጆች በዚያ ነበሩ።+ የእስራኤልን ሕዝብ ለመባረክ (የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ቀደም ሲል ባዘዘው መሠረት)+ ግማሾቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት፣ ግማሾቹ ደግሞ በኤባል ተራራ ፊት ለፊት ቆሙ።+ 34 ከዚህ በኋላ ኢያሱ በሕጉ መጽሐፍ+ ላይ በተጻፈው መሠረት የሕጉን ቃላት በሙሉ ይኸውም በረከቱንና+ እርግማኑን+ ድምፁን ከፍ አድርጎ አነበበ።
-