-
ዘዳግም 13:6-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 “የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ አሊያም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ጓደኛህ* ‘ሌሎች አማልክትን እናምልክ’+ በማለት በሚስጥር ሊያባብልህ ቢሞክርና እነዚህ አማልክት ደግሞ አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸው 7 እንዲሁም በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ የሚገኙ በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸው አማልክት ቢሆኑ 8 እሺ አትበለው ወይም አትስማው+ አሊያም አትዘንለት ወይም ደግሞ አትራራለት፤ ከለላም አትሁነው፤ 9 ከዚህ ይልቅ ያለማመንታት ግደለው።+ እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጅህን መሰንዘር ያለብህ አንተ ነህ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ይሰንዝርበት።+
-