-
ዘዳግም 13:12-15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 “አምላክህ ይሖዋ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ትሰማ ይሆናል፦ 13 ‘እናንተ የማታውቋቸውን “ሌሎች አማልክት ሄደን እናምልክ” እያሉ የከተማቸውን ነዋሪዎች ለማሳት የሚሞክሩ የማይረቡ ሰዎች ከመካከልህ ተነስተዋል’፤ 14 በዚህ ጊዜ ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመርና በማጣራት ስለ ሁኔታው ማወቅ ይኖርብሃል፤+ ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ ተፈጽሞ ከሆነና ነገሩ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ 15 የከተማዋን ነዋሪዎች በሰይፍ ግደላቸው።+ እንስሶቿን ጨምሮ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ በሰይፍ ሙሉ በሙሉ አጥፋ።+
-