-
1 ሳሙኤል 28:7-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 በመጨረሻም ሳኦል አገልጋዮቹን “መናፍስት ጠሪ+ ፈልጉልኝ፤ እኔም ሄጄ ምክር እጠይቃታለሁ” አላቸው። አገልጋዮቹም “በኤንዶር+ አንዲት መናፍስት ጠሪ አለች” በማለት መለሱለት።
8 በመሆኑም ሳኦል ማንነቱን ሰውሮና ሌላ ልብስ ለብሶ ከሁለት ሰዎች ጋር በመሆን በሌሊት ወደ ሴትየዋ ሄደ። እሱም “እባክሽ፣ መናፍስትን ጠርተሽ+ ጠንቁይልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት። 9 ሆኖም ሴትየዋ እንዲህ አለችው፦ “ሳኦል መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድሪቱ በማስወገድ ምን እንዳደረገ አንተ ራስህ በሚገባ ታውቃለህ።+ ታዲያ እኔ እንድገደል ልታጠምደኝ* የምትሞክረው ለምንድን ነው?”+ 10 ከዚያም ሳኦል “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ በዚህ ጉዳይ በጥፋተኝነት አትጠየቂም!” በማለት በይሖዋ ማለላት። 11 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ “እሺ ማንን ላስነሳልህ?” አለችው። እሱም “ሳሙኤልን አስነሺልኝ” አላት።
-