-
ዘኁልቁ 21:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ከዘረድ ሸለቆ ተነስተው ከአሞራውያን ድንበር ጀምሮ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በሚገኘው በአርኖን ክልል+ ሰፈሩ፤ ምክንያቱም አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ድንበር ነው።
-
-
መሳፍንት 11:17, 18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ከዚያም እስራኤል ለኤዶም+ ንጉሥ “እባክህ ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን” ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላከ፤ የኤዶም ንጉሥ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። ለሞዓብም+ ንጉሥ መልእክት ላኩ፤ እሱም ቢሆን በዚህ ሐሳብ አልተስማማም። ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ+ ተቀመጠ። 18 በምድረ በዳው በተጓዙበት ጊዜ በኤዶም ምድርና በሞዓብ ምድር ዳርቻ አልፈው ሄዱ።+ ከሞዓብ ምድር በስተ ምሥራቅ ተጉዘውም+ በአርኖን ክልል ሰፈሩ፤ ወደ ሞዓብ ወሰንም አልገቡም፤+ ምክንያቱም አርኖን የሞዓብ ወሰን ነበር።
-