ዘዳግም 19:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ዳኞቹም ጉዳዩን በጥንቃቄ ይመረምራሉ፤+ ምሥክሩ ሐሰተኛ ምሥክር ከሆነና ወንድሙን የወነጀለው በሐሰት ከሆነ 19 በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ነገር በራሱ ላይ አድርጉበት፤+ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+ ዘዳግም 21:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና+ ሰካራም+ ነው’ ይበሏቸው። 21 ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ።+
18 ዳኞቹም ጉዳዩን በጥንቃቄ ይመረምራሉ፤+ ምሥክሩ ሐሰተኛ ምሥክር ከሆነና ወንድሙን የወነጀለው በሐሰት ከሆነ 19 በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ነገር በራሱ ላይ አድርጉበት፤+ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+
20 ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና+ ሰካራም+ ነው’ ይበሏቸው። 21 ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ።+