-
ዘዳግም 15:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+
-
-
ሉቃስ 6:38አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
38 ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል።+ ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።”
-
-
2 ቆሮንቶስ 9:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ይሁንና ጥቂት የሚዘራ ሁሉ ጥቂት ያጭዳል፤ በብዛት የሚዘራ ሁሉ ደግሞ በብዛት ያጭዳል።+
-
-
1 ዮሐንስ 3:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ቁሳዊ ንብረት ያለው ሰው ወንድሙ ሲቸገር ተመልክቶ ሳይራራለት ቢቀር ‘የአምላክ ፍቅር በእሱ ውስጥ አለ’ እንዴት ሊባል ይችላል?+
-