የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 17:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መታሰቢያ* እንዲሆን ይህን በመጽሐፍ ጻፈው፤ ለኢያሱም ‘የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ’+ በማለት ይህን ደግመህ ንገረው።”

  • 1 ሳሙኤል 14:47, 48
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 47 ሳኦልም በእስራኤል ላይ ንግሥናውን አጸና፤ በዙሪያው ከነበሩት ጠላቶቹ ማለትም ከሞዓባውያን፣+ ከአሞናውያን፣+ ከኤዶማውያን፣+ ከጾባህ+ ነገሥታትና ከፍልስጤማውያን+ ጋር ተዋጋ፤ በሄደበትም ሁሉ ድል ያደርጋቸው ነበር። 48 እንዲሁም በጀግንነት በመዋጋት አማሌቃውያንን+ ድል አደረገ፤ እስራኤላውያንንም ከዘራፊዎቻቸው እጅ አዳነ።

  • 1 ሳሙኤል 15:1-3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ እንድቀባህ የላከው እኔን ነበር፤+ እንግዲህ አሁን ይሖዋ ምን እንደሚል ስማ።+ 2 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ ጊዜ በመንገድ ላይ እነሱን በመቃወም ለፈጸሙት ድርጊት አማሌቃውያንን እቀጣቸዋለሁ።+ 3 በል አሁን ሂድ፤ አማሌቃውያንን+ ምታቸው፤ እነሱንም ካላቸው ነገር ሁሉ ጋር ፈጽመህ አጥፋቸው።+ አንዳቸውንም አታስቀር፤* ወንድም ሆነ ሴት፣ ልጅም ሆነ ሕፃን፣ በሬም ሆነ በግ፣ ግመልም ሆነ አህያ ሁሉንም ግደል።’”+

  • 1 ዜና መዋዕል 4:42, 43
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 42 ከስምዖናውያን መካከል የተወሰኑት ይኸውም 500 ወንዶች በይሽኢ ወንዶች ልጆች በጰላጥያህ፣ በነአርያህ፣ በረፋያህ እና በዑዚኤል መሪነት ወደ ሴይር+ ተራራ ወጡ። 43 እነሱም ከአማሌቃውያን+ መካከል አምልጠው የቀሩትን ሰዎች መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይኖራሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ