30 ኢያሱም በኤባል ተራራ+ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ መሠዊያ የሠራው በዚያን ጊዜ ነበር፤ 31 መሠዊያውንም የሠራው የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ለእስራኤላውያን በሰጠው ትእዛዝና በሙሴ የሕግ መጽሐፍ+ ላይ በተጻፈው “መሠዊያው የብረት መሣሪያ ካልነካው ያልተጠረበ ድንጋይ የተሠራ ይሁን”+ በሚለው መመሪያ መሠረት ነው። በዚያም ላይ የሚቃጠሉ መባዎችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን ለይሖዋ አቀረቡ።+
32 ከዚያም በድንጋዮቹ ላይ ሙሴ በእስራኤላውያን ፊት የጻፈውን ሕግ ቅጂ+ ጻፈባቸው።+