3 ለሙሴ በገባሁት ቃል መሠረት እግራችሁ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ እሰጣችኋለሁ።+ 4 ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስና እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ይኸውም መላው የሂታውያን+ ምድር እንዲሁም በስተ ምዕራብ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል።+ 5 በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም።+ ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ሁሉ ከአንተም ጋር እሆናለሁ።+ አልጥልህም ወይም አልተውህም።+