-
ኢያሱ 10:3-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በመሆኑም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ለኬብሮን+ ንጉሥ ለሆሐም፣ ለያርሙት ንጉሥ ለፒራም፣ ለለኪሶ ንጉሥ ለያፊአ እና ለኤግሎን ንጉሥ+ ለደቢር እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ 4 “መጥታችሁ እርዱኝና በገባኦን ላይ ጥቃት እንሰንዝር፤ ምክንያቱም ገባኦን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ፈጥራለች።”+ 5 በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን+ ነገሥታት ይኸውም የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬብሮን ንጉሥ፣ የያርሙት ንጉሥ፣ የለኪሶ ንጉሥና የኤግሎን ንጉሥ ከነሠራዊታቸው አንድ ላይ ተሰብስበው በመዝመት ገባኦንን ለመውጋት ከበቧት።
-