የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 13:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 በመሆኑም አብራም ሄደ፤ በድንኳን መኖሩንም ቀጠለ። ከጊዜ በኋላም በኬብሮን+ ወደሚገኙት የማምሬ+ ትላልቅ ዛፎች መጥቶ መኖር ጀመረ፤ በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ።+

  • ዘፍጥረት 23:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 ከዚያ በኋላ አብርሃም ሚስቱን ሣራን በማምሬ ይኸውም በከነአን ምድር ባለው በኬብሮን ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ የእርሻ ቦታ ውስጥ ባለው ዋሻ ቀበራት።

  • ዘኁልቁ 13:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 በኔጌብ በኩል ሽቅብ ሲወጡም ኤናቃውያኑ+ አሂማን፣ ሸሻይ እና ታልማይ+ ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን+ ደረሱ። ኬብሮን የተቆረቆረችው በግብፅ ያለችው ጾዓን ከመቆርቆሯ ከሰባት ዓመት በፊት ነበር።

  • ኢያሱ 10:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 በመሆኑም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ለኬብሮን+ ንጉሥ ለሆሐም፣ ለያርሙት ንጉሥ ለፒራም፣ ለለኪሶ ንጉሥ ለያፊአ እና ለኤግሎን ንጉሥ+ ለደቢር እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ 4 “መጥታችሁ እርዱኝና በገባኦን ላይ ጥቃት እንሰንዝር፤ ምክንያቱም ገባኦን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ፈጥራለች።”+

  • ኢያሱ 15:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ኢያሱ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ በይሁዳ ዘሮች መካከል የምትገኘውን ኬብሮን+ የተባለችውን ቂርያትአርባን ድርሻ አድርጎ ሰጠው (አርባ የኤናቅ አባት ነበር)።

  • ኢያሱ 21:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ለካህኑ ለአሮን ልጆችም ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ+ የሆነችውን ኬብሮንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ሊብናን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ