-
ኢያሱ 13:2-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 የሚቀረውም ምድር ይህ ነው፦+ የፍልስጤማውያንና የገሹራውያን+ ምድር በሙሉ 3 (ከግብፅ ፊት ለፊት ከሚገኘው ከአባይ ወንዝ ቅርንጫፍ* አንስቶ በሰሜን እስከ ኤቅሮን ወሰን ድረስ ያለው ክልል የከነአናውያን ግዛት እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር)+ እንዲሁም በጋዛ፣ በአሽዶድ፣+ በአስቀሎን፣+ በጌት+ እና በኤቅሮን+ የሚኖሩትን የአምስቱን የፍልስጤም ገዢዎች+ ምድር የሚጨምር ሲሆን የአዊም+ ሰዎችንም ምድር ያካትታል፤ 4 እነሱም በደቡብ በኩል ይኖሩ ነበር፤ መላው የከነአናውያን ምድር፤ የሲዶናውያን+ ይዞታ የሆነችው መአራ፣ እንዲሁም በአሞራውያን ወሰን ላይ እስከሚገኘው እስከ አፌቅ ድረስ ያለው አካባቢ፤ 5 የጌባላውያን+ ምድር፣ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ያለው መላው ሊባኖስ ይኸውም በሄርሞን ተራራ ግርጌ ከሚገኘው ከበዓልጋድ አንስቶ እስከ ሌቦሃማት*+ ድረስ ያለው አካባቢ፤ 6 በተራራማው አካባቢ፣ ከሊባኖስ+ እስከ ሚስረፎትማይም+ ባለው ምድር የሚኖሩት ነዋሪዎች በሙሉ እንዲሁም ሲዶናውያን+ በሙሉ ናቸው። እነሱንም ከእስራኤላውያን ፊት አባርራቸዋለሁ።+ አንተም ባዘዝኩህ መሠረት ምድሩን ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ ስጥ።+
-