6 ምክንያቱም ይሖዋ የሶርያውያን ሰፈር የጦር ሠረገሎችን ድምፅ፣ የፈረሶችን ድምፅና የታላቅ ሠራዊት ድምፅ እንዲሰማ አድርጎ ነበር።+ በመሆኑም እርስ በርሳቸው “የእስራኤል ንጉሥ እኛን ለመውጋት የሂታውያንንና የግብፅን ነገሥታት ቀጥሮብናል!” ተባባሉ። 7 እነሱም ወዲያውኑ ተነስተው በምሽት ሸሹ፤ ድንኳኖቻቸውን፣ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም ሰፈሩን እንዳለ ትተው ሕይወታቸውን ለማዳን እግሬ አውጪኝ አሉ።