መሳፍንት 14:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እነሱም ባዩት ጊዜ አብረውት እንዲሆኑ 30 ሚዜዎችን አመጡ። መሳፍንት 15:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወቅት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደ። እሱም “ሚስቴ ወዳለችበት መኝታ ቤት* መግባት እፈልጋለሁ” አለ። አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። 2 ከዚያም አባትየው እንዲህ አለው፦ “እኔ እኮ ‘ፈጽሞ ጠልተሃታል’ ብዬ አስቤ ነበር።+ ስለሆነም ለሚዜህ ዳርኳት።+ ታናሽ እህቷ ከእሷ ይልቅ ቆንጆ አይደለችም? እባክህ በዚያችኛዋ ፋንታ ይህችኛዋን አግባት።”
15 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወቅት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደ። እሱም “ሚስቴ ወዳለችበት መኝታ ቤት* መግባት እፈልጋለሁ” አለ። አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። 2 ከዚያም አባትየው እንዲህ አለው፦ “እኔ እኮ ‘ፈጽሞ ጠልተሃታል’ ብዬ አስቤ ነበር።+ ስለሆነም ለሚዜህ ዳርኳት።+ ታናሽ እህቷ ከእሷ ይልቅ ቆንጆ አይደለችም? እባክህ በዚያችኛዋ ፋንታ ይህችኛዋን አግባት።”