-
መሳፍንት 15:4, 5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ሳምሶንም ሄዶ 300 ቀበሮዎችን ያዘ። ከዚያም ችቦዎች አመጣ፤ ቀበሮዎቹንም ፊታቸውን አዙሮ ጭራና ጭራቸውን አንድ ላይ ካሰረ በኋላ በጭራቸው መሃል አንድ አንድ ችቦ አደረገ። 5 በመቀጠልም ችቦዎቹን በእሳት በመለኮስ ቀበሮዎቹን በፍልስጤማውያን እርሻ ላይ ባለው ያልታጨደ እህል ውስጥ ለቀቃቸው። ከነዶው አንስቶ እስካልታጨደው እህል ድረስ እንዲሁም የወይን እርሻዎችንና የወይራ ዛፎችን አቃጠለ።
-