-
1 ሳሙኤል 6:3, 4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ያለመባ እንዳትመልሱት። ከበደል መባ ጋር አድርጋችሁ ወደ እሱ መመለስ ይኖርባችኋል።+ የምትፈወሱት እንዲህ ካደረጋችሁ ብቻ ነው፤ ደግሞም እጁ ከእናንተ ላይ ያልተመለሰው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ።” 4 ስለዚህ “ወደ እሱ መላክ የሚኖርብን የበደል መባ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁ። እነሱም እንዲህ አሏቸው፦ “እናንተንም ሆነ ገዢዎቻችሁን ያሠቃየው መቅሰፍት ተመሳሳይ ስለሆነ በፍልስጤም ገዢዎች+ ቁጥር ልክ አምስት የወርቅ ኪንታሮቶችንና* አምስት የወርቅ አይጦችን ላኩ።
-