1 ነገሥት 10:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የሳባ ንግሥት ስለ ሰለሞን ዝና እንዲሁም ከይሖዋ ስም ጋር ስላለው ግንኙነት ሰማች፤+ በመሆኑም አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች* ልትፈትነው መጣች።+ 1 ነገሥት 10:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ከዚያም ለንጉሡ 120 ታላንት* ወርቅ እንዲሁም እጅግ ብዙ የበለሳን ዘይትና+ የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው።+ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰለሞን የሰጠችውን የሚያህል መጠን ያለው የበለሳን ዘይት ከዚያ በኋላ መጥቶ አያውቅም። 2 ዜና መዋዕል 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤+ የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለኢዮሳፍጥ ስጦታ ያመጡለት ነበር፤ እሱም ብዙ ሀብትና ታላቅ ክብር አገኘ።+
10 ከዚያም ለንጉሡ 120 ታላንት* ወርቅ እንዲሁም እጅግ ብዙ የበለሳን ዘይትና+ የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው።+ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰለሞን የሰጠችውን የሚያህል መጠን ያለው የበለሳን ዘይት ከዚያ በኋላ መጥቶ አያውቅም።