የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መሳፍንት 3:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት።

  • መሳፍንት 6:34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 የይሖዋም መንፈስ በጌድዮን ላይ ወረደ፤* + እሱም ቀንደ መለከት ነፋ፤+ አቢዔዜራውያንም+ እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ።

  • መሳፍንት 11:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ።

  • መሳፍንት 14:5, 6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ስለዚህ ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ። በቲምና ወዳለው የወይን እርሻ ሲደርስም አንድ ደቦል አንበሳ እያገሳ መጣበት። 6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም።

  • 1 ሳሙኤል 10:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በመሆኑም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታው ሄዱ፤ አንድ የነቢያት ቡድንም አገኘው። ወዲያውም የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እሱም አብሯቸው ትንቢት መናገር ጀመረ።+ 11 ቀደም ሲል ያውቁት የነበሩት ሁሉ ከነቢያቱ ጋር ሆኖ ትንቢት ሲናገር ሲያዩት እርስ በርሳቸው “የቂስ ልጅ ምን ሆኗል? ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ?” ተባባሉ።

  • 1 ሳሙኤል 16:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው።+ በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ+ ሄደ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ