-
1 ዜና መዋዕል 12:39, 40አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
39 ወንድሞቻቸው አዘጋጅተውላቸው ስለነበር በዚያ እየበሉና እየጠጡ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ቆዩ። 40 በተጨማሪም በአቅራቢያቸው ያሉትም ሆኑ እስከ ይሳኮር፣ ዛብሎንና ንፍታሌም ድረስ ርቀው የሚገኙት ሰዎች በአህያ፣ በግመል፣ በበቅሎና በከብት ምግብ ጭነው መጡ፤ ይኸውም ከፍተኛ መጠን ያለው ዱቄት፣ የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣ የወይን ጠጅ፣ ዘይት፣ ከብትና በግ ነበር፤ በእስራኤል ታላቅ ደስታ ሰፍኖ ነበርና።
-