2 ሳኦል ከእስራኤላውያን መካከል 3,000 ሰዎችን መረጠ፤ ከእነዚህም መካከል 2,000ዎቹ በሚክማሽና በቤቴል ተራራማ አካባቢ ከሳኦል ጋር ሆኑ፤ ሌሎቹ 1,000 ሰዎች ደግሞ በቢንያም ግዛት በጊብዓ+ ከዮናታን+ ጋር ሆኑ። የቀሩትን ሰዎች እያንዳንዳቸውን ወደየድንኳናቸው አሰናበታቸው። 3 ዮናታንም በጌባ+ የነበረውን የፍልስጤማውያንን+ የጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሩ ሁሉ ቀንደ መለከት አስነፋ።+