-
ዘፍጥረት 17:9, 10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 በተጨማሪም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “በአንተ በኩል፣ አንተም ሆንክ ከአንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮችህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ቃል ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ። 10 እናንተም ሆናችሁ ከእናንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮቻችሁ ልትጠብቁት የሚገባው በእኔና በእናንተ መካከል ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፦ በእናንተ መካከል ያለ ወንድ ሁሉ መገረዝ አለበት።+
-
-
መሳፍንት 14:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ሆኖም አባቱና እናቱ “ከዘመዶችህና ከእኛ ሕዝብ መካከል ለአንተ የምትሆን ሴት አጥተህ ነው?+ የግድ ሄደህ ካልተገረዙት ፍልስጤማውያን መካከል ሚስት ማግባት አለብህ?” አሉት። ሳምሶን ግን አባቱን “ልቤን የማረከችው እሷ ስለሆነች እሷን አጋባኝ” አለው።
-
-
መሳፍንት 15:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ከዚያም በጣም ተጠማ፤ ወደ ይሖዋም እንዲህ ሲል ጮኸ፦ “ይህ ታላቅ መዳን በአገልጋይህ እጅ እንዲፈጸም ያደረግከው አንተ ነበርክ። ታዲያ አሁን በውኃ ጥም ልሙት? በእነዚህ ባልተገረዙ ሰዎች እጅስ ልውደቅ?”
-
-
1 ሳሙኤል 17:36አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
36 አገልጋይህ አንበሳውንም ሆነ ድቡን ገድሏል፤ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጤማዊም ሕያው በሆነው አምላክ ሠራዊት ላይ ስለተሳለቀ መጨረሻው ከእነሱ እንደ አንዱ ይሆናል።”+
-