-
1 ሳሙኤል 17:38, 39አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
38 ከዚያም ሳኦል ለዳዊት የራሱን ልብሶች አለበሰው። በራሱም ላይ ከመዳብ የተሠራ ቁር ደፋለት፤ ጥሩርም አለበሰው። 39 በኋላም ዳዊት ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጥቆ ለመራመድ ሞከረ፤ ሆኖም ከዚህ በፊት እንደዚህ ዓይነት ትጥቅ ታጥቆ ስለማያውቅ መራመድ አልቻለም። ዳዊትም ሳኦልን “እንዲህ ያሉ ትጥቆችን ታጥቄ ስለማላውቅ እነሱን አድርጌ መራመድ አልቻልኩም” አለው። በመሆኑም ዳዊት ከላዩ ላይ አወለቃቸው።
-