-
1 ሳሙኤል 25:14-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢጋኤል እንዲህ አላት፦ “እነሆ፣ ዳዊት ለጌታችን መልካም ምኞቱን ለመግለጽ መልእክተኞችን ከምድረ በዳ ልኮ ነበር፤ እሱ ግን የስድብ ናዳ አወረደባቸው።+ 15 ሰዎቹ ለእኛ እጅግ ጥሩ ነበሩ። ምንም ዓይነት ጉዳት አድርሰውብን አያውቁም፤ በመስክ ከእነሱ ጋር አብረን በነበርንባቸው ጊዜያት ሁሉ አንድም ነገር ጠፍቶብን አያውቅም።+ 16 መንጋውን እየጠበቅን ከእነሱ ጋር በቆየንባቸው ጊዜያት ሁሉ ሌሊትም ሆነ ቀን በዙሪያችን እንደ መከላከያ ቅጥር ሆነውልን ነበር።
-