-
1 ሳሙኤል 11:9-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 የመጡትንም መልእክተኞች እንዲህ አሏቸው፦ “በጊልያድ ባለችው በኢያቢስ የሚኖሩትን ሰዎች ‘በነገው ዕለት ፀሐይዋ በምትከርበት ጊዜ መዳን ታገኛላችሁ’ በሏቸው።” ከዚያም መልእክተኞቹ መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሯቸው፤ እነሱም በደስታ ፈነደቁ። 10 ስለሆነም የኢያቢስ ሰዎች “ነገ እጃችንን ለእናንተ እንሰጣለን፤ እናንተም መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ልታደርጉብን ትችላላችሁ” አሏቸው።+
11 በማግስቱ ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ቡድን ከፈለው፤ እነሱም በማለዳው ክፍለ ሌሊት* ወደ አሞናውያን+ ሰፈር ገብተው ፀሐይዋ እስክትከር ድረስ መቷቸው። የተረፉትም ቢሆኑ ሁለቱ እንኳ አንድ ላይ መሆን እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ።
-