2 ሳሙኤል 2:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ከዚህ በኋላ ዳዊት “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዱ ልውጣ?” በማለት ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም “ውጣ” አለው። ዳዊትም “ወዴት ብሄድ ይሻላል?” አለ። እሱም “ወደ ኬብሮን”+ አለው። 2 ሳሙኤል 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ዳዊት በኬብሮን ንጉሥ ሆኖ በይሁዳ ቤት ላይ የገዛበት ጊዜ* ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበር።+ 1 ዜና መዋዕል 12:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የሳኦልን ንግሥና ወደ ዳዊት ለማስተላለፍ በኬብሮን+ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት የመጡት ለውጊያ የታጠቁ መሪዎች ቁጥር ይህ ነው።+
2 ከዚህ በኋላ ዳዊት “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዱ ልውጣ?” በማለት ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም “ውጣ” አለው። ዳዊትም “ወዴት ብሄድ ይሻላል?” አለ። እሱም “ወደ ኬብሮን”+ አለው።