-
1 ዜና መዋዕል 19:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ከጊዜ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናሃሽ ሞተ፤ በእሱም ፋንታ ልጁ ነገሠ።+ 2 በዚህ ጊዜ ዳዊት “አባቱ ታማኝ ፍቅር+ ስላሳየኝ እኔም ለናሃሽ ልጅ ለሃኑን ታማኝ ፍቅር አሳየዋለሁ” አለ። በመሆኑም ዳዊት በአባቱ ሞት ከደረሰበት ሐዘን እንዲያጽናኑት መልእክተኞችን ላከ። ሆኖም የዳዊት አገልጋዮች ሃኑንን ለማጽናናት ወደ አሞናውያን+ ምድር ሲደርሱ 3 የአሞናውያን መኳንንት ሃኑንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አጽናኞችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃል? አገልጋዮቹ ወደ አንተ የመጡት ምድሪቱን በሚገባ ለማጥናትና በውስጧ ያለውን ነገር ለመሰለል እንዲሁም አንተን ለመገልበጥ አይደለም?” 4 በመሆኑም ሃኑን የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ ላጫቸው፤+ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ላካቸው። 5 በአገልጋዮቹ ላይ የደረሰውን ነገር ለዳዊት በነገሩት ጊዜ ሰዎቹ በኀፍረት ተውጠው ስለነበር ዳዊት ወዲያውኑ መልእክተኞችን ወደ እነሱ ላከ፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ+ ቆዩ፤ ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።
-