-
ዘፀአት 1:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 አዋላጆቹም ፈርዖንን “ዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፃውያን ሴቶች አይደሉም። እነሱ ብርቱዎች ስለሆኑ አዋላጇ ከመድረሷ በፊት በራሳቸው ይወልዳሉ” አሉት።
-
-
ኢያሱ 2:3-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በዚህ ጊዜ የኢያሪኮ ንጉሥ ወደ ረዓብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከባት፦ “ቤትሽ መጥተው ያረፉትን ሰዎች አውጪ፤ ምክንያቱም ወደዚህ የመጡት ምድሪቱን በሙሉ ለመሰለል ነው።”
4 ሴትየዋ ግን ሁለቱን ሰዎች ደበቀቻቸው። ከዚያም እንዲህ አለች፦ “በእርግጥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተው ነበር፤ ሆኖም ከየት እንደመጡ አላወቅኩም። 5 ምሽት ላይ የከተማዋ በር ሊዘጋ ሲል ወጥተው ሄደዋል። ወዴት እንደሄዱ አላውቅም፤ ሆኖም ፈጥናችሁ ከተከታተላችኋቸው ልትደርሱባቸው ትችላላችሁ።”
-
-
1 ሳሙኤል 19:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 ሜልኮልም ዳዊት ሸሽቶ እንዲያመልጥ ወዲያውኑ በመስኮት አሾልካ አወረደችው።
-
-
1 ሳሙኤል 19:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት መልእክተኞችን ላከ፤ እሷ ግን “አሞታል” አለቻቸው።
-
-
1 ሳሙኤል 21:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ዳዊትም ለካህኑ ለአሂሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ንጉሡ አንድ ጉዳይ እንዳስፈጽም አዞኝ ነበር፤ ሆኖም ‘ስለሰጠሁህ ተልእኮና ስላዘዝኩህ ነገር ማንም ሰው ምንም ነገር እንዳያውቅ’ ብሎኛል። ከሰዎቼም ጋር የሆነ ቦታ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረናል።
-