17 ከዚያም አኪጦፌል አቢሴሎምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ 12,000 ሰዎች ልምረጥና ተነስቼ ዛሬ ማታ ዳዊትን ላሳደው። 2 በደከመውና አቅም ባጣ ጊዜ ድንገት እደርስበታለሁ፤+ ሽብርም እለቅበታለሁ፤ አብረውት ያሉት ሰዎችም ሁሉ ይሸሻሉ፤ ንጉሡን ብቻ እመታለሁ።+ 3 ከዚያም ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ። የሕዝቡ ሁሉ መመለስ የተመካው አንተ የምትፈልገው ሰው በሚደርስበት ነገር ላይ ነው። ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ሰላም ያገኛል።”