-
1 ዜና መዋዕል 11:15-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 የፍልስጤም ሠራዊት በረፋይም ሸለቆ*+ ሰፍሮ በነበረበት ጊዜ፣ ከ30ዎቹ መሪዎች መካከል ሦስቱ ዓለታማ ወደሆነውና ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ አዱላም ዋሻ ወረዱ።+ 16 በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበር፤ የፍልስጤማውያንም ሠራዊት በቤተልሔም ነበር። 17 ከዚያም ዳዊት “በቤተልሔም+ በር አቅራቢያ ካለው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ የምጠጣው ውኃ ባገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ!” በማለት ምኞቱን ገለጸ። 18 በዚህ ጊዜ ሦስቱ ወደ ፍልስጤማውያን ሰፈር ጥሰው በመግባት በቤተልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውኃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ ዳዊት ግን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ውኃውን ለይሖዋ አፈሰሰው። 19 እንዲህም አለ፦ “ለአምላኬ ካለኝ አክብሮት የተነሳ ይህን ማድረግ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው! ሕይወታቸውን* አደጋ ላይ ጥለው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም ልጠጣ ይገባል?+ ውኃውን ያመጡት በሕይወታቸው* ቆርጠው ነውና።” በመሆኑም ውኃውን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም። ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎቹ ያደረጓቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ።
-