-
1 ዜና መዋዕል 21:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ከዚያም ሰይጣን* እስራኤልን ለማጥቃት ቆርጦ ተነሳ፤ ደግሞም እስራኤልን እንዲቆጥር ዳዊትን አነሳሳው።+ 2 በመሆኑም ዳዊት ኢዮዓብንና+ የሕዝቡን አለቆች “ሂዱና ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ዳን+ ድረስ ያሉትን እስራኤላውያን ቁጠሩ፤ ከዚያም ቁጥራቸውን አውቅ ዘንድ ንገሩኝ” አላቸው። 3 ኢዮዓብ ግን እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሕዝቡን 100 እጥፍ ያብዛው! ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ሁሉም የጌታዬ አገልጋዮች አይደሉም? ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን ፈለገ? በእስራኤልስ ላይ ለምን በደል ያመጣል?”
-