-
1 ዜና መዋዕል 21:18-23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 በዚህ ጊዜ የይሖዋ መልአክ፣ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርናን አውድማ ላይ ለይሖዋ መሠዊያ እንዲሠራ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን+ አዘዘው።+ 19 ዳዊትም ጋድ በይሖዋ ስም በነገረው ቃል መሠረት ወጣ። 20 ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦርናን ዞር ሲል መልአኩን አየው፤ ከእሱ ጋር የነበሩት አራት ወንዶች ልጆቹም ተሸሸጉ። በዚህ ጊዜ ኦርናን ስንዴ እየወቃ ነበር። 21 ኦርናን ቀና ብሎ ሲመለከት ዳዊት ወደ እሱ ሲመጣ አየ፤ ወዲያውኑም ከአውድማው ወጥቶ በግንባሩ መሬት ላይ በመደፋት ለዳዊት ሰገደ። 22 ዳዊትም ኦርናንን እንዲህ አለው፦ “ለይሖዋ መሠዊያ እንድሠራበት አውድማውን ሽጥልኝ።* በሕዝቡ ላይ የሚወርደው መቅሰፍት እንዲቆም+ ሙሉውን ዋጋ ከፍዬ ልግዛው።” 23 ኦርናን ግን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በነፃ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሡ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ። እነሆ ከብቶቹን ለሚቃጠል መባ፣ ማሄጃውን*+ ለማገዶ፣ ስንዴውን ደግሞ ለእህል መባ አቀርባለሁ። ሁሉንም ነገር እኔ እሰጣለሁ።”
-