-
መሳፍንት 9:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 እነሱም ከባአልበሪት+ ቤት* 70 የብር ሰቅል ሰጡት፤ አቢሜሌክም ተከታዮቹ እንዲሆኑ በዚህ ገንዘብ ሥራ ፈቶችንና ወሮበሎችን ቀጠረበት። 5 ከዚያም በኦፍራ+ ወደሚገኘው ወደ አባቱ ቤት ሄዶ ወንድሞቹን ማለትም 70ዎቹን የየሩባአል ልጆች በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው።+ በሕይወት የተረፈው የሁሉም ታናሽ የሆነው የየሩባአል ልጅ ኢዮዓታም ብቻ ነበር፤ ምክንያቱም እሱ ተደብቆ ነበር።
6 ከዚያም የሴኬም መሪዎች ሁሉ እንዲሁም የቤትሚሎ ሰዎች በሙሉ በአንድነት ተሰብስበው በመሄድ አቢሜሌክን በትልቁ ዛፍ አጠገብ ይኸውም በሴኬም በነበረው ዓምድ አጠገብ አነገሡት።+
-
-
1 ነገሥት 1:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 አለዚያ ግን ጌታዬ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰለሞን እንደ ከዳተኞች ተደርገን እንቆጠራለን።”
-