-
2 ዜና መዋዕል 10:1-4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 እስራኤላውያን በሙሉ ሮብዓምን ለማንገሥ ወደ ሴኬም+ መጥተው ስለነበር እሱም ወደ ሴኬም ሄደ።+ 2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ ይህን እንደሰማ (ምክንያቱም በወቅቱ ኢዮርብዓም ከንጉሥ ሰለሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበር)፣+ ከግብፅ ተመልሶ መጣ። 3 ከዚያም ሰዎች ልከው አስጠሩት፤ ኢዮርብዓምና መላው እስራኤልም መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት፦ 4 “አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር።+ አንተ ግን አባትህ የሰጠንን አስቸጋሪ ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ* ቀንበር የምታቀልልን ከሆነ እናገለግልሃለን።”
-