የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 14:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በዚህም የተነሳ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋት አመጣለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን ጨምሮ የኢዮርብዓም የሆነውን ወንድ* ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ አንድ ሰው ፋንድያን ሙልጭ አድርጎ በመጥረግ እንደሚያስወግድ ሁሉ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ!+

  • 1 ነገሥት 15:25-29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ናዳብ+ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ እሱም በእስራኤል ላይ ለሁለት ዓመት ገዛ። 26 በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ገፋበት፤ የአባቱንም መንገድ ተከተለ፤+ እንዲሁም አባቱ እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረገው ኃጢአት ተመላለሰ።+ 27 ከይሳኮር ቤት የሆነው የአኪያህ ልጅ ባኦስ በእሱ ላይ አሴረ፤ ናዳብና እስራኤል ሁሉ የፍልስጤማውያን ከተማ የሆነችውን ጊበቶንን+ ከበው ሳሉ ባኦስ ጊበቶን ላይ ናዳብን ገደለው። 28 በመሆኑም ባኦስ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ናዳብን ገድሎ በምትኩ ነገሠ። 29 እሱም እንደነገሠ ወዲያውኑ የኢዮርብዓምን ቤት ሁሉ ፈጀ። ከኢዮርብዓም ቤት እስትንፋስ ያለውን አንድም ሰው አላስቀረም፤ ይሖዋ በአገልጋዩ በሴሎናዊው በአኪያህ በኩል በተናገረው መሠረት ሁሉንም ደመሰሳቸው።+

  • 2 ነገሥት 17:22, 23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 የእስራኤልም ሰዎች ኢዮርብዓም የፈጸማቸውን ኃጢአቶች ሁሉ ሠሩ።+ ከዚያ ዞር አላሉም፤ 23 ይህም የሆነው ይሖዋ በአገልጋዮቹ በነቢያት ሁሉ አማካኝነት በተናገረው መሠረት እስራኤልን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ ነው።+ በመሆኑም እስራኤላውያን ከገዛ ምድራቸው ወደ አሦር በግዞት ተወሰዱ፤+ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ