12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+ 13 ከዚያም በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ።+ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሰለሞን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ የሠራቸውን የወርቅ ዕቃዎች በሙሉ ሰባበራቸው።+ ይህ የሆነው ይሖዋ አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው።