-
2 ዜና መዋዕል 16:11-14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለው የአሳ ታሪክ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል።+
12 አሳ በ39ኛው የግዛት ዘመኑ እግሩን ታመመ፤ ሕመሙም ጠናበት፤ ታሞ ሳለም እንኳ የባለ መድኃኒቶችን እንጂ የይሖዋን እርዳታ አልፈለገም። 13 በመጨረሻም አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በ41ኛው የግዛት ዘመኑም ሞተ። 14 እነሱም በዳዊት ከተማ+ ለራሱ ባስቆፈረው ታላቅ የመቃብር ቦታ ቀበሩት፤ የበለሳን ዘይት እንዲሁም ከተለያዩ ቅመሞች የተዘጋጀ ልዩ ቅባት በሞላበት ቃሬዛ ላይ አኖሩት።+ በተጨማሪም ለክብሩ ታላቅ እሳት አነደዱለት።*
-