23 እንግዲህ አሁን ሁለት ወይፈኖች ይስጡን፤ እነሱም አንድ ወይፈን መርጠው በየብልቱ እየቆራረጡ በእንጨቱ ላይ ያድርጉት፤ ሆኖም እሳት አያንድዱበት። እኔ ደግሞ ሌላኛውን ወይፈን አዘጋጅቼ በእንጨቱ ላይ አደርገዋለሁ፤ ሆኖም እሳት አላነድበትም። 24 ከዚያም እናንተ የአምላካችሁን ስም ትጠራላችሁ፤+ እኔም የይሖዋን ስም እጠራለሁ። እሳት በመላክ መልስ የሚሰጠው አምላክ እሱ እውነተኛው አምላክ እንደሆነ ያሳያል።”+ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “ያልከው ነገር ጥሩ ነው” አሉ።