-
2 ነገሥት 9:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከዚያም ነቢዩ ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ልብስህን በወገብህ ታጠቅና ይህን የዘይት ዕቃ ይዘህ ወደ ራሞትጊልያድ+ በፍጥነት ሂድ። 2 እዚያም ስትደርስ የኒምሺን ልጅ፣ የኢዮሳፍጥን ልጅ ኢዩን+ ፈልገው፤ ከዚያም ገብተህ ከወንድሞቹ መካከል አስነሳውና ወደ ውስጠኛው ክፍል ውሰደው። 3 የዘይቱንም ዕቃ ወስደህ ዘይቱን በራሱ ላይ አፍስ፤ እንዲህም በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።”’+ ከዚያም በሩን ከፍተህ በፍጥነት ሽሽ።”
-
-
2 ነገሥት 9:30-33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል+ መጣ፤ ኤልዛቤልም+ ይህን ሰማች። በመሆኑም ዓይኖቿን ተኩላና ፀጉሯን አሰማምራ በመስኮት ቁልቁል ትመለከት ጀመር። 31 ኢዩም በቅጥሩ በር በኩል ሲገባ ኤልዛቤል “ጌታውን የገደለው ዚምሪ ምን እንደደረሰበት አታውቅም?” አለችው።+ 32 እሱም ወደ መስኮቱ ቀና ብሎ በመመልከት “ከእኔ ጎን የቆመ ማን ነው? ማን ነው?”+ አለ። ወዲያውኑ ሁለት ወይም ሦስት የሚሆኑ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ቁልቁል ተመለከቱት። 33 እሱም “ወደ ታች ወርውሯት!” አላቸው። እነሱም ወረወሯት፤ ደሟም በግድግዳውና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በፈረሶቹ ረጋገጣት።
-