25 ኢዩም የጦር መኮንኑን ቢድቃርን እንዲህ አለው፦ “አንስተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ ላይ ጣለው።+ እኔና አንተ በሠረገሎች ሆነን አባቱን አክዓብን እንከተለው በነበረ ጊዜ ይሖዋ ራሱ በእሱ ላይ ይህን ፍርድ እንዳስተላለፈ አስታውስ፦+ 26 ‘“ትናንት የናቡቴን ደምና የልጆቹን ደም እንዳየሁ ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፣ “በዚህ የእርሻ ቦታ ላይ ዋጋህን እከፍልሃለሁ”+ ይላል ይሖዋ።’ በመሆኑም ይሖዋ በተናገረው ቃል መሠረት አንስተህ እርሻው ላይ ጣለው።”+