7 አንተም የጌታህን የአክዓብን ቤት ትመታለህ፤ እኔም የአገልጋዮቼን የነቢያትን ደምና በኤልዛቤል እጅ የሞቱትን የይሖዋን አገልጋዮች ሁሉ ደም እበቀላለሁ።+ 8 የአክዓብም ቤት በጠቅላላ ይጠፋል፤ ደግሞም በእስራኤል ውስጥ ያለውን ምስኪኑንም ሆነ ደካማውን ጨምሮ ከአክዓብ ቤት ወንድ የተባለውን ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ።+ 9 የአክዓብንም ቤት እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤትና+ እንደ አኪያህ ልጅ እንደ ባኦስ ቤት+ አደርገዋለሁ።