2 ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም በሰማርያ ወደሚገኘው ወደ አክዓብ ወረደ፤+ አክዓብም ለኢዮሳፍጥና አብረውት ለነበሩት ሰዎች እጅግ ብዙ በግና ከብት መሥዋዕት አደረገ። ደግሞም በራሞትጊልያድ+ ላይ እንዲዘምት ገፋፋው። 3 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “ወደ ራሞትጊልያድ ከእኔ ጋር አብረህ ትሄዳለህ?” አለው። እሱም “እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ፤ ሕዝቤም ሕዝብህ ነው፤ በጦርነቱም አብረንህ እንሰለፋለን” አለው።