-
ኢያሱ 20:8, 9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ ባለው የዮርዳኖስ ክልል ደግሞ ከሮቤል ነገድ ርስት በአምባው ላይ በሚገኘው ምድረ በዳ ላይ ያለችውን ቤጼርን፣+ ከጋድ ነገድ ርስት በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትን+ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ ርስት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን+ መረጡ።+
9 ሳያስበው ሰው* የገደለ ማንኛውም ግለሰብ በማኅበረሰቡ ፊት ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት ደም ተበቃዩ አግኝቶ እንዳይገድለው ሸሽቶ እንዲሸሸግባቸው+ ለእስራኤላውያን በሙሉ ወይም በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው የተለዩት ከተሞች እነዚህ ናቸው።+
-
-
1 ነገሥት 4:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 ሰለሞን በመላው እስራኤል ላይ የተሾሙ ለንጉሡና ለቤተሰቡ ቀለብ የሚያቀርቡ 12 አስተዳዳሪዎች ነበሩት። እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር።+
-