-
2 ነገሥት 4:32-35አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
32 ኤልሳዕ ወደ ቤት ሲገባ ልጁ ሞቶ በእሱ አልጋ ላይ ተጋድሞ አገኘው።+ 33 ከዚያም ወደ ውስጥ ገብቶ በሩን በራሱና በልጁ ላይ ከዘጋ በኋላ ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀመረ።+ 34 ከዚያም አልጋው ላይ ወጥቶ ልጁ ላይ በመተኛት አፉን በአፉ፣ ዓይኑን በዓይኑ እንዲሁም መዳፉን በመዳፉ ላይ አድርጎ ላዩ ላይ ተደፋበት፤ የልጁም ሰውነት መሞቅ ጀመረ።+ 35 ኤልሳዕ ተነስቶ ቤቱ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይል ጀመር፤ ደግሞም እንደገና አልጋው ላይ ወጥቶ ላዩ ላይ ተደፋበት። ልጁም ሰባት ጊዜ ካስነጠሰው በኋላ ዓይኖቹን ገለጠ።+
-