-
2 ነገሥት 2:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 እሱም ከኤልያስ ላይ በወደቀው የነቢይ ልብስ ውኃውን መታና እንዲህ አለ፦ “የኤልያስ አምላክ ይሖዋ የት አለ?” ውኃውንም ሲመታው ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።+
-
-
2 ነገሥት 4:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከዚያም ገብተሽ በሩን በአንቺና በልጆችሽ ላይ ዝጊው። ዕቃዎቹንም ሁሉ በዘይት ሙዪ፤ የሞሉትንም ለብቻ አስቀምጫቸው።”
-
-
2 ነገሥት 4:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 እሷም ሄዳ ለእውነተኛው አምላክ ሰው ነገረችው፤ እሱም “ሂጂ፤ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን ክፈዪ፤ የተረፈው ደግሞ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ ይሁን” አላት።
-
-
2 ነገሥት 6:5-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ከእነሱ አንዱ ዛፍ እየቆረጠ ሳለ የመጥረቢያው አናት ወልቆ ውኃው ውስጥ ወደቀ። ሰውየውም “ወየው ጌታዬ፣ ተውሼ ያመጣሁት መጥረቢያ እኮ ነው!” በማለት ጮኸ። 6 የእውነተኛው አምላክ ሰውም “የት ነው የወደቀው?” አለው። ሰውየውም ቦታውን አሳየው። እሱም እንጨት ቆርጦ ውኃው ውስጥ በመጣል የመጥረቢያው አናት እንዲንሳፈፍ አደረገ። 7 ከዚያም “በል አውጣው” አለው። ሰውየውም እጁን ዘርግቶ ወሰደው።
-