የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 26:16-21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ይሁን እንጂ ዖዝያ በበረታ ጊዜ ለጥፋት እስኪዳረግ ድረስ ልቡ ታበየ፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ በመግባት በአምላኩ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጸመ።+ 17 ወዲያውኑም ካህኑ አዛርያስና ደፋር የሆኑ ሌሎች 80 የይሖዋ ካህናት ተከትለውት ገቡ። 18 ከዚያም ንጉሥ ዖዝያን ፊት ለፊት በመጋፈጥ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ፣ አንተ ለይሖዋ ዕጣን ማጠንህ ተገቢ አይደለም!+ ዕጣን ማጠን ያለባቸው ካህናቱ ብቻ ናቸው፤ እነሱ የተቀደሱ የአሮን ዘሮች ናቸውና።+ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ስለፈጸምክ ከመቅደሱ ውጣ፤ እንዲህ ማድረግህ በይሖዋ አምላክ ዘንድ ምንም ዓይነት ክብር አያስገኝልህም።”

      19 ዕጣን ለማጠን በእጁ ጥና ይዞ የነበረው ዖዝያ ግን እጅግ ተቆጣ፤+ ካህናቱን እየተቆጣ ሳለም በይሖዋ ቤት በዕጣን መሠዊያው አጠገብ ካህናቱ ባሉበት ግንባሩ ላይ የሥጋ ደዌ+ ወጣበት። 20 የካህናቱ አለቃ አዛርያስና ካህናቱ ሁሉ ባዩት ጊዜ ግንባሩ በሥጋ ደዌ ተመቶ ነበር! በመሆኑም ከዚያ አጣድፈው አስወጡት፤ እሱ ራሱም ይሖዋ ስለመታው ለመውጣት ቸኩሎ ነበር።

      21 ንጉሥ ዖዝያ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የሥጋ ደዌ በሽተኛ ሆኖ ኖረ፤ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በመሆኑ በአንድ የተለየ ቤት ውስጥ ተገልሎ ተቀመጠ፤+ ወደ ይሖዋ ቤት እንዳይገባ ታግዶ ነበር። ልጁ ኢዮዓታም በንጉሡ ቤት* ላይ ተሹሞ በምድሪቱ በሚኖረው ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ